Andode Secondary School
Announcement የተማሪዎች ጥያቄ እና መልስ ውድድር

የተማሪዎች ጥያቄ እና መልስ ውድድር

27th May, 2025

በአንዶዴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከ11/09/2017 እስከ 15/09/2017 ዓ.ም በ Mathematics እና English  የትምህርት አይነቶች  የተማሪዎች ጥያቄ እና መልስ ውድድር ተካሂዷል። የተማሪዎችን የእርስ በርስ አወንታዊ የፉክክር መንፈስ በማሳደግ በእንግሊዝኛ እና ሒሳብ ትምህርት ውጤታቸውን ከፍ ለማድረግ እና ለማሻሻል ዓላማው አድርጎ በተከናወነው የጥያቄ እና መልስ ውድድር እጅግ አስደናቂ የአልሸነፍ ባይነት ፉክክር የታየበት ነበር ። በየ ውድድሮቹ በአንደኛው መንፈቅ ዓመት ከየክፍላቸው  ደረጃ ይዘው ያጠናቀቁ  ተማሪዎች ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን ያደረጉት ፉክክርም ደረጃቸውን የሚመጥን ነበር ። በአጠቃላይ በተደረገው ውድድር በየክፍል ደረጃው ከ1-3ኛ የወጡ ተማሪዎች የተለዩ ሲሆን በቀጣይ የማበረታቻ  ሽልማት የሚበረከትላቸው ይሆናል። 🏅🏅🏅🏅🏅🏅🏅🏅
    በእንግሊዝኛ  እና ሒሳብ ትምህርቶች የተደረገው ውድድር በቴክኖሎጂ የተደገፈ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል። 🧑‍💻
በየ ውድድሮች የት/ቤታችን ርዕሳነ መምህራን እየተገኙ ምልከታ አድርገዋል። 

👉ጥያቄ በማውጣትና በመጠየቅ ፤በማስተባበርና በዳኝነት የተሳተፋችሁ ሁሉ ትመሰገናላችሁ ።  በተለይም እነዚህን ድንቅ ድንቅ ተማሪዎች ያፈራችሁ መምህራን ምስጋና ያንስቧችኋል 👏👏👏👏👏👏

የተማሪዎችን ተወዳዳሪነት በማሳደግ ለውጤታማነት እንተጋለን ‼

በአንዶዴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የጥያቄ እና መልስ ውድድር ኮሚቴ

.

Copyright © All rights reserved.

Created with